በምግብ እሴት ሰንሰለት ውስጥ የምግብ ደህንነትን ማረጋገጥ፣ ደህንነታቸው ያልተጠበቁ ምግብ መንስኤዎች፣ የበሽታው ስርጭትና ጫና እንዲሁም የተቀናጀ የቅኝት ስርዕት ዙሪያ ትኩረቱን ያደረገ የግንዛቤ ማስጨበጫ መድረክ ተካሂዷል።
በመድረኩ የምግብ ደህንነትና የምግብ ወለድ በሽታዎች አጠቃላይ እይታና የኢትዮጽያ የምግብ ወለድ በሽታዎች ቅኝት ፕሮጀክት የሚያከናወናቸው ተግባራትን የሚያሳያ ጽሁፍ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።
የሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ ቺፍ ኤግዚኪዩቲቭ ዳይሬክተር ዶ/ር አህመድ መሐመድ ባደረጉት የመክፈቻ ንግግር ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ በግብርና ፣ በጤናና በማህበረሰብ ምርምር ዘርፍ በሀገር አቀፍ ደረጃ ለሚወጡ ፖሊሲዎች ግብዓት የሚሆኑ የምርምር ውጤቶችን እያበረከተ እንደሚገኝ ገልጸው በምግብ ደህንነትና በምግብ ወለድ በሽታዎች ዙሪያ ከሀገር ውስጥና ከውጭ አጋር ተቋማት ጋር በቅንጅት እየሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የምግብ ወለድ በሽታ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ የጤና ቀውስ እየሆነ እንደመጣና 723 ሚለዮን ዶላር ዓመታዊ ኪሳራና ከጠቅላላ የሀገር ውስጥ ምርት (GDP) 0.9% ለመቀነስ ምክንያት እየሆነ መምጣቱን ዓለም አቀፍ ጥናቶች እንደሚያሳዩ በመድረኩ ተገልጿል።
በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ጤናና ህክምና ሳይንስ ኮሌጅ መምህርና ተመራማሪ የሆኑት ዶ/ር ደሳለኝ አድማሱ በበኩላቸው በምግብ ወለድ በሽታዎችና በሀገር አቀፍ ደረጃ እየተከናወነ ስላለው የተቀናጀ የቅኝት ስርዓት ዙሪያ ከሐረርጌ ጤናና ስነ-ህዝብ ስርዓተ-ቅኝት የማህበረሰብ አማካሪዎችና ለባለድርሻ አካላት ግንዛቤ ለመፍጠርና ቀጣይ አቅጣጫ ለማስቀመጥ መድረኩ መዘጋጀቱን ገልጸዋል።
የመድረኩ ተሳታፊዎች በሰጡት አስተያየት ከግንዛቤ ማስጨበጫ መድረኩ በምግብ ወለድ በሽታዎችና የቅኝት ስርዓት ዙሪያ ግንዛቤ እንዳገኙ ገልጸው ያገኙትን እውቀት ለሰፊው ማህበረሰብ በማካፈል ለምግብ ደህንነት መረጋገጥ የበኩላቸውን አስተዋጾ እንደሚያበረክቱ ቃል ገብተዋል።